Skip to main content

ነገረ ማሪያም

እመቤታችን ቅድስት ድንግል  ማሪያም  በንጽሕና:በቅድስና:በሞገስ ና በጸጋ በክብር የሚመስላት ሆነ የሚያህላት የሌለ: እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የያዘች:ከሆነ ጀምሮ በአዳም ልጅነቷ ንጽሐ ጠባይ ያላደፈባት:በዚህ ዓለም ኑሮዋም ከሀልዮ:ከነቢብ ና ከገቢር ኃጢአት ንጽሕት የሆነች:ከቅዱሳን ሁሉ በላይ ጸጋን የተሞላች:ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች:በአማላጅነቷ:የምዕመናን ሁሉ መማጸኛ የሆነች የአምላክ  እናት ናት።(ሉቃ1:27-30:ሕዝ44:3-5,መኃ4:7:መዝ132:13:ኢሳ7:14).


ስለንጽሕናዋ:ቴዎዶጦስ/ሃይ.አበ53:32

ስለ ክብሯ ታላቅነት:ዮሐንስ አፈወርቅ/ሃይ.አበ28:36-39 እና ሌሎችም አበው የተናገሩትን ይመለከቱ።

በዚህ ምክንያት 

ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ

ምልዕተ ጸጋ:ምልዕተ ክብር

እመ አምላክ:ወላዲተ አምላክ:እመ እግዚአብሔር 

ሰአሊተ ምሕረት 

ድንግል በክልኤ

ቅድስተ ቅዱሳን

መትሕተ ፈጠሪ መልእልተ ፍጡራን  ወዘተ እየተባለች ትጠራለች።


ለዚህም ምንጩ የወንጌል  ውዳሴ ማሪያም ነው።

ሉቃ1:26-5:ዮሐ 19:25-28 ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ።


የታወቀው የቅዳሴ ማሪያም ደራሲ አባ ሕርያቆስ"ወስሉጥ ስመኪ በኅበ እግዚአብሔር "ሲል ሲናገር የኢትዮጵያ  ቤተ ክርስቲያን  ለእመቤታችን  የተሰጠ ቃል ኪዳንና ክብር ከሁሉም ቅዱሳን በላይ መሆኑን ታምናለች።ታስተምራለች።

በመሆኑ በማንኛውም  ጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ስሟ በተማኅጽኖ ይጠራል።

ከዚህ ጋር በኢትዮጵያ  ሆነ በሌላው የክርስትና  ዓለም በጸሎት ሆነ በትምህርት  ስሟ ሳይጠራ የሚውልበት  ዕለት የለም።


ወስብሐት  ለእግዚአብሔር ።

Comments

Popular posts from this blog

Free skill course

 Free 'Skills' Courses a.  Learn copywriting 1. youtu.be/Pum2gV7N_9A 2. youtu.be/9qZcT9I8W4g 3. youtu.be/B13gAAcqrAc 4. youtu.be/UfCgUv8-HlI 5. youtu.be/LU4gHGdYDI0 b. Learn photography 1. youtu.be/yhAmMUi2NmM 2. youtu.be/LxO-6rlihSg 3. youtu.be/V7z7BAZdt2M c. Learn video editing 1. youtu.be/y7Ci_H9bYEk 2. youtu.be/oC3gXr1s_aU 3. youtu.be/ZQDGJn89uNk 4. youtu.be/MqwlW76sFCM d. Learn to proofread 1. youtu.be/Up3WZJn4OpQ 2. youtu.be/sNbi3h7Ucr0 3. youtu.be/pYb7p0DiVMI 4. youtu.be/14pgya2Xl8o e. Learn transcription 1. youtu.be/bltDLL6-CbQ f. Learn public speaking 1. youtu.be/i5mYphUoOCs 2. youtu.be/dHAbmoFHqgA 3. youtu.be/7tzentBmmUc 4. youtu.be/k8GvTgWtR7o g. Learn digital marketing 1. youtu.be/hiEb1m7CXH4 2. youtu.be/BjRmz6rO9SQ g. Learn digital marketing 1. youtu.be/hiEb1m7CXH4 2. youtu.be/BjRmz6rO9SQ h. Learn web development 1. youtu.be/Q33KBiDriJY  2. youtu.be/zAfLvFHKUS0 I. Learn graphic designing 1. youtu.be/9QTCvayLhCA 2. youtu.be/k0EyAs9Q4NI j. Learn game developmen...

Python Road map

 

Maths Cheat sheet for data science