Skip to main content

ነገረ ክርሰቶስ

 🌹ድርሳነ 🌹ቄርሎስ 🌹መግቢያ 🌹ክፍል ፩ 

ቅዱሳት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር እየተባሉ ይጠራሉ። ቅዱስ ቄርሎስ በኤፌሶን ጉባዔ ለ200ው ሊቃውንት አፈ ጉባዔ የነበረና ንስጥሮስን የረታ ታላቅ ሊቅ ነው። ይህ ቄርሎስ ትምህርት በጀመረ በአምስት ዓመቱ የብሉይ ኪዳንንና የሐዲስ ኪዳንን ትርጓሜ ተምሮ ያጠናቀቀ ቅዱስ ሊቅ ነው። ሲያስተምርም ከአንደበቱ ርቱዕነት ከጣዕመ ቃሉ ፍጹምነት ከትምህርተ ጥቅሱ ምሥጢርና ከምክሩ ከተግሣፁ የተነሣ የሚሰሙት ሁሉ ትምህርቱን አቋርጦ ይተውብን ይሆን ምነው ቢጨምርበት እያሉ ልቡናቸውን በተመሥጦ ሰቅለው ሕሊናቸውን አቅንተው ይሰሙት ነበር እንጂ አይሰለቹትም ነበር። ስመ ሥርጋዌው (የክብር ስሙ) መምህረ ዓለም ይባላል።


ቅዱስ ቄርሎስ ይህንን መጽሐፍ የጻፈው ከጉባዔ ኤፌሶን ጀምሮ ባለው ጊዜ ነው። ይህ መጽሐፍ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን ወልደ ማርያም ወልደ አብ መሆኑን ያስረዳል። ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ በሥጋ መሆኗን ይገልጻል። ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ መሆኑን ያስረዳል። ይህ መጽሐፍ ውስጥ ለብዙ ከሓድያን ምላሽ ይሰጣል።

    ፩፦ የክርስቶስ ሥጋ ምትሐት ነው ለሚል ለማኒ

    ፪፦ ቃል ወደ ሥጋ ተለወጠ ለሚሉ ለሐራ ጥቃ

    ፫፦ የቃል መነሻ ከማርያም ወዲህ ነው ለሚሉ

    ፬፦ የቃል አካል አልነበረውም ለሚሉ 

    ፭፦ ለሥጋ በነፍስ ምትክ መለኮት ሆነው ለሚሉ

    ፮፦ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ለሚሉ

እና ለመሳሰሉት ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ነው። የቃል መነሻ ከማርያም ወዲህ ነው የሚሉ እነ ፎጢኖስ ናቸው። ክርስቶስ ነፍስ የለውም በነፍሱ ምትክ መለኮቱ ሆነው የሚሉ እነ አቡሊናርዮስ ናቸው። ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ የሚል ንስጥሮስ ነው። ቃል ዝርው ነው አካል አልነበረውም የሚሉ እነ መርቅያን ናቸው።


ድርሳነ ቄርሎስን መማር ለሚፈልጉ ሼር አድርጉላቸው። ድርሳነ ቄርሎስ በደንብ ግልጽ እንዲሆንላችሁ በተከታታይነት የተማማርነውን ሃይማኖተ አበው በPDF ከዚህ ፖስት በፊት ያገኙታል።


© በትረማርያም አበባው




🌻ድርሳነ 🌻ቄርሎስ 🌻ክፍል ፪


ቄርሎስ ማለት አንበሳ ኃያል ኅሩይ (የተመረጠ፣ ምርጥ) ማለት ነው። አንበሳ መባሉ መ*ፍቃ*ንን እንደ አንበሳ በኃይለ ቃል ይሰብራቸዋልና ነው። የቅዱስ ቄርሎስን እናት ያሳደገቻት ኢትዮጵያዊት አገልጋይ ናት። ይህች ኢትዮጲያዊት መጀመሪያ ጣዖት አምላኪ ነበረች። በኋላ ቅዱስ አትናቴዎስን አጥምቀኝ ብላው ተጠምቃለች። ቴዎፍሎስ ሲሞት በእርሱ ምትክ ቅዱስ ቄርሎስ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኗል። ቅዱስ ቄርሎስ አፈጉባዔ ሆኖ የረታው መና*ቅ ንስጥሮስ ነው።


ንስጥሮስ የዲያድርስ የአጎቱ ልጅ ነው። ዲያድርስ የጳውሎስ ሳምሳጢ ደቀ መዝሙር ነው። ዲያድርስ ክሕደቱን ከጳውሎስ ሳምሳጢ ተማረ። ንስጥሮስ ደግሞ ክሕደቱን ከዲያድርስ ተማረ። ጳውሎስ ሳምሳጢ ግን ክሕደቱን ከዲያብሎስ ተምሮታል። ንስጥሮስ ከዲያድርስ የተማረውን ክሕደት ፕትርክና ሲሾም ገለጠው። አንዱን ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ነው አለ። ቅዱስ ቄርሎስ ይህንን በሰማ ጊዜ አከራክረኝ ብሎ ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ላከበት።


ንጉሡም በኤፌሶን ጉባዔ እንዲሆን አዘዘ። 200 ሊቃውንት በአንድነት ሆነው ንስጥሮስን አውግዘው ለይተውታል። ቅዱስ ቄርሎስ በመዓርጉ ከሐዋርያት ከነቢያት የደረሰ ነበር። ንስጥሮስን ክሕደትን የካደች ምላስህ አትታዘዝህ ቢለው ምላሱ ተጎሎጉሎ ወጥቶ እንደውሻ ጓጉሮ ሞቷል። ቅዱሳን ምንም ባይከራከሩ ከጉባዔ አይለዩም። ቄርሎስ ምሥጢረ ተዋሕዶን በነበልባልና በሐመልማል፣ በእሳትና በብረት፣ በነፍስና በሥጋ ተዋሕዶ እየመሰለ ያስተምር ነበር።


© በትረማርያም አበባው





https://t.me/betremariyamabebaw/3862





🌷ድርሳነ 🌷ቄርሎስ 🌷ክፍል ፫

                     ❤️ምዕራፍ ፩

በዚህ መጽሐፍ እስከ ምጽአት የሚነሱ ሊቃውንት መ*ና*ቃንን ሲረቱበት ይኖራሉ። ትክክለኛዋ ሃይማኖት ክርስቶስን አንድ አካል አንድ ባሕርይ የምትል ናት። ሰውን ጻድቅ ቢሉት ሐሰት፣ ንጹሕ ቢሉት ኃጢአት፣ ባዕል ቢሉት ንዴት ይስማማዋል። እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ዘአልቦ ሐሰት፣ ንጹሕ ዘአልቦ ኃጢአት፣ ባዕል ዘአልቦ ንዴት ነው።

                       ❤️ምዕራፍ ፪

ናባል ዳዊት መጣ ቢሉት ደንግጦ እንደሞተ ሁሉ ነቢያት ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል ብለው ሲያስተምሩ አጋንንት ይወጡ ነበረ። ዳዊት ኢዮአብን አቢሳን እየሰደደ ድል ያደርግ እንደነበረ ጌታም ነቢያትን እየሰደደ አጋንንትን ያስወጣ ነበረ።

                       ❤️ምዕራፍ ፫

በአራቱ መዓዝን ምሉዕ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና እንዲገባ ለቅዱሳንም የአክብሮት ስግደት መስገድ ይገባል። የሀብተ መንግሥት አስገኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ በእውነተኛ ሃይማኖት ጸንተው ለሚወዱት ሰዎች ክህነትን መንግሥትን ፈጽሞ ይሰጣል።

                       ❤️ምዕራፍ ፬

ነገሥታት አምልኮተ እግዚአብሔርን ቢይዙ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጣቸው የጸጋ ክብር አለ። ከእግዚአብሔር ትእዛዝ መውጣት አይገባም። አምላክ ሥነ ፍጥረትን የፈጠረ ለሰው ነው።

                      ❤️ምዕራፍ ፭

ሰናክሬም በትዕቢት ሆኖ እግዚአብሔርን ተሳደበ። ንጉሡ ሕዝቅያስ ጌታ ሲሰደብ ሰምቶ ልብሱን ቀደደ አሰለበ። ልብስን መቅደድ የኀዘን ምልክት ነው።  (እግዚአብሔር ሲሰደብ፣ ቤተክርስቲያን ስትሰደብ ማዘን ይገባል)።

                      ❤️ምዕራፍ ፮

ሕዝቅያስ ጌታ ሲሰደብ በማዘኑ ጠላትን የማሸነፍ ሀብትን ከእግዚአብሔር ዘንድ አገኘ። ብዙ ሠራዊት የነበረው ሰናክሬምንም አሸነፈው። እግዚአብሔርን የማምለክ ፍሬው ይህ ነው። እኛ ምክንያት ሆነን እግዚአብሔርን ማሰደብ አይገባንም።

                      ❤️ምዕራፍ ፯

ንጉሥ አኖሬዎስ ንጹሕ ድንግል ነው። ዐቢይ ጾምን ገዳመ አስቄጥስ እየሄደ ይጾም ነበር። ሐሰት የሌለባት አንድ አካል አንድ ባሕርይ የምትል ሃይማኖትን ለነፍሳችሁ ጌጥ አድርጓት። ሃይማኖት የልቡና መደገፊያ፣ የሰውነት ተድላ ደስታ፣ የራስ ዘውድ ናት።


© በትረ ማርያም አበባው










Comments

Popular posts from this blog

Python Road map

 

Command on Run

 🔰 23 Important Commands in the RUN (Executer) List 🔹 The command dxdiag: Used to check all the specifications of your device.   🔹 The command cleanmgr: Opens the Disk Cleanup tool.   🔹 The command temp: Accesses temporary files, which we delete as they contribute to slowing down the computer.   🔹 The command regedit: Opens the Registry Editor.   🔹 The command calc: Opens the Calculator.   🔹 The command msconfig: A tool to access programs that run with Windows at startup and disable them to speed up the system.   🔹 The command scandisk: Used for disk checking.   🔹 The command cmd: Opens the Command Prompt for Windows.   🔹 The command defrag: Used to stop and defragment the hard drive.   🔹 The command taskman: Allows you to see what is open in the taskbar and manage it.   🔹 The command pbrush: Opens the Paint program in Windows.   🔹 The command debug: Used to ch...

Is it the end of lora?

 Is this the end of LoRA as a fine-tuning approach? Singular Value fine-tuning is here! We have a new paper in town called the "Transformers Squared". It promises to adapt any LLM to any task without external intervention.  The core idea of the paper is to use Singular Value Decomposition (SVD) to factorize the weight matrices of transformers. During training, we learn different singular values for different tasks. More specifically, we learn to scale the singular values for different tasks. Tasks can be as diverse as math reasoning or coding. The possibilities are endless. During inference, we do a two-pass inference. In the first pass, the LLM decides which "scale" to use for which task. In the second pass, the LLM adapts itself to be a specialist in the task and responds to our prompt. How cool is that? Paper Title: Transformer2: Self-adaptive LLMs Paper: https://sakana.ai/transformer-squared Blog: https://arxiv.org/abs/2501.06252 Video Explanation: https://youtu...