Skip to main content

የዕለቱ ወንጌል ሐምሌ 5

 05/11/2016 /ጴጥሮስ ወጳውሎስ ብርሃናተ ዓለም 72 አርድእት ወይስሐቅ ሰማእት/

                      የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                         ዮሐንስ 21:15-20


     ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” አለው። “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው።“ግልገሎቼን አሰማራ፡” አለው። ደግሞ ሁለተኛ፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው። “አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ፡” አለው። “ጠቦቶቼን ጠብቅ፡” አለው። ሦስተኛ ጊዜ፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ፦ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ፡” አለው። ኢየሱስም አለው፦ “በጎቼን አሰማራ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ አንተ ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል።” በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን አለ። ይህንም ብሎ፦ “ተከተለኝ፡” አለው።

           የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት
                        1 ተሰሎንቄ 4:13-ፍጻሜ

   ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን። ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና። በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን። ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

2 ጴጥሮስ 1:1-13
ሐዋ.ሥራ 23:10:16

                          ምስባክ
                    መዝሙር138:17-18


ወኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ

ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ

እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ

Comments

Popular posts from this blog

Python Road map

 

Command on Run

 🔰 23 Important Commands in the RUN (Executer) List 🔹 The command dxdiag: Used to check all the specifications of your device.   🔹 The command cleanmgr: Opens the Disk Cleanup tool.   🔹 The command temp: Accesses temporary files, which we delete as they contribute to slowing down the computer.   🔹 The command regedit: Opens the Registry Editor.   🔹 The command calc: Opens the Calculator.   🔹 The command msconfig: A tool to access programs that run with Windows at startup and disable them to speed up the system.   🔹 The command scandisk: Used for disk checking.   🔹 The command cmd: Opens the Command Prompt for Windows.   🔹 The command defrag: Used to stop and defragment the hard drive.   🔹 The command taskman: Allows you to see what is open in the taskbar and manage it.   🔹 The command pbrush: Opens the Paint program in Windows.   🔹 The command debug: Used to ch...