ሐምሌ 09/11/2013:
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ሉቃስ 13:18-23
እርሱም፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት ምን ትመስላለች፥ በምንስ አስመስላታለሁ? ሰው ወስዶ በአትክልቱ የጣላትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤ አደገችም ታላቅ ዛፍም ሆነች፥ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ ሰፈሩ፡” አለ። ደግሞም፦ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን አስመስላታለሁ? ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች፡” አለ። ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ከተማዎችንና መንደሮችን እያስተማረ ያልፍ ነበር....
1ኛ ጢሞ3:1-11
1 ጴጥ 5:1-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 20:28-31
፳፰በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።፳፱-፴ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።፴፩ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ"
ምስባክ
መዝሙር 83:6
እስመ መምህረ ህግ ይሁብ በረከተ
ወየኃውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን
ትርጉም
የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና
ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል
Comments
Post a Comment