ሐምሌ 15 :የቅዱስ ኤፍሬም የእረፍቱ በዓል ነው።
አፈ በረከት ማር ኤፍሬም 14ሺ መጽሐፍን እንደዴረሰ ይነገራል።
መጽሐፍን እውነተኛ ጓድኛ እያሉ ብዙዎች ቢገልጹትም።
ግን እንደ ቅዱስ ኤፍሬም አድርገው አልገለጹትም::
ቅዱስ ኤፍሬም እንድህ ገልጾታል
በእውነት የውስጥን ገላልጦ የሚያሳይ መስታውት:በእውነት ትናንትን ዛሬ አድርጎ የሚያሳይ መስታውት:ትቢያ የማይበንበት ጢስ የማይተንበት ለዘለዓለም ንጹሕ መስታውት:በእውነት ቁመናን ሳይሆን አቋምን የሚያሳይ መስታውት
በእውነት ያልኖሩትን ዓለም ያልተዋቡበትን ጌጥ በማሳየት እርግጠኛ አድርጎ በማሳየት ዛሬ የያዙትን ጣፋጭ ሕይወት የሚያስንቅ ድንቅ መስታውት:
የዓይናችንን ጉድፍ የጥርሳችንን እድፍ ሳይደብቅ እንደሚያሳይ መስታወት።
ታላቁ መስታውት መጽሐፍ።
ምንጭ:ፍትሐ ነገሥት ምን አለ?
አንቀጽ 2 መምህር በጽሐ ዓለሙ
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 4:17-21
፲፯የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።፲፰በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።፲፱እርሱም። በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።፳ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።፳፩ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም::
ምንባባት:
ኤፌ 5:7-21
ያዕቆብ 5:12-17
የሐዋ 9:22-30
ምስባክ
መዝሙር 88(89):6-7
መኑ ይትዔየሮ ለእግዚአብሔር በደመናት
ወመኑ ይመስሎ ለእግዚአብሔር እንደቂቀ አማልእክት
እግዚአብሔር ስቡሕ በምክረ ቅዱሳን
Comments
Post a Comment