Skip to main content

ራስን መግዛት

 የስሜት ሕዋሳቶቻችንና ክርስትና


መምህር ቢትወደድ ወርቁ


ሰው በልዩ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሲገኝ የሚሰማውን ስሜት በስሜት ሕዋሳቱ አማካኝነት ይገልጣቸዋል፡፡ ደስታ፣ ቁጣ፣ ፍርሃት፣ ሕመም፣ ፍቅር እና የመሳሰሉት ስሜቶቻችን ናቸው፡፡ ሰው እነዚህን ስሜቶቹን በስሜት ሕዋሳቱ በዐይኑ፣ በእጁ፣ በእግሩ፣ በአንደበቱ፣ በፊት ገጽታውና በሰውነት እንቅስቃሴው ይገልጣል፡፡ እነዚህ ስሜቶች ከሚቀሰቀሱበት ሁነቶች፣ ድርጊቶችና ክስተቶች አንጻር በፍጥነት ምላሽ ሳይሰጥ ነገሮችን በዕርጋታ የሚመረምር ሰው በሳል ወይም ባለ አእምሮ ይባላል፡፡ በተቃራኒው ለጉዳዮች ፈጣን ምላሽ የሚሰጠውን ደግሞ ስሜታዊ እንለዋለን፡፡ ባለ አእምሮ ሰው በመረጋጋቱ ብዙ ሲያተርፍ ስሜታዊ ሰው ግን የሚያጸጽቱና ግላዊ፣ ማኅበራዊ እንዲሁም ሀገራዊ ጥፋቶችን የሚያስከትሉ ዋጋዎችን ይከፍላል፡፡ በመሆኑም መጽሐፍ “እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ” በማለት ያስተምረናል፡፡ (፩ኛጴጥ.፬፥፯-፰)

በስሜት ሕዋሳቶቻችን ለምንገልጣቸው ድርጊቶቻችንና ምላሾቻችን ጥንቃቄ እንድናደርግ ቅዱሳት መጻሕፍት በእጅጉ ያስጠነቅቁናል፡፡ ለምሳሌም ጠቢቡ ሰሎሞን “በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል”፤ “ከንፈሩን የሚነ*ክስ ክፋትን ይፈጽማል” በማለት አከታትሎ የተናገራቸው ቃላት ይህንኑ ያስተምሩናል፡፡ (ምሳ.፲፥፲፣ ምሳ.፲፮፥፴) ዓይን የስሜት ሕዋስ ሲሆን ጥቅሻ ደግሞ ለአንድ ድርጊት የምንሰጠው ምላሽ ነው፡፡ ከንፈርን መን*ከስ የብስጭት፣ የቁጣና በአንድ ጉዳይ የመብገን ምልክት ነው፡፡ ከንፈሩን የነ*ከሰ ሰው ፈጥኖ ወደ ሕሊናው ካልተመለስ ቀጣይ እርምጃው ከንፈሩን የነከሰበትን ሰው መን*ከስ፣ ማጥ*ቃት ወይም ደግሞ አንዳች ክፉ ነገር ማድረግ ይሆናል፡፡


ስሜት በሚወልደው በአንድ ድርጊት ምክንያት የሚሰጥ ምላሽ ጥንቃቄ ካልታከለበት መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ስለሆነም በደስታ ጊዜ ፈጥኖ ቃል መግባት፣ በቁጣ ጊዜ ፈጥኖ የቃልና የተግባር ምላሽ መስጠት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ከደስታ ስሜት ስንወጣ “እንዲህ ያልኩት ምን ነክቶኝ ነው?” ብለን በማሰብ እንድንሸማቀቅና ቃል ለገባንላትም አካል “አላልኩም” ብለን ልቡን እንሰብራለን፡፡ የስሜት ምላሻችን ማኅበራዊ ኑሯአችንን ከማበላሸቱም ባሻገር ለከኑኔ ያደርሳል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል “ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው፡፡ ከልብ ክፉ አሳብ፣ መግ*ደል፣ ምንዝርነት፣ ዝሙት፣ መስ*ረቅ፣ በውሸት መመስከር፣ ስድብ ነው” ብሎ የተናገረውን ቃለ ትምህርት እናስተውል፡፡ (ማቴ.፲፭፥፲፰)


ከአፍ የምናወጣው ስድ*ብ የስሜታዊነት ምላሽ ነው፤ መግ*ደልም ሰዎች ለፈጸሙብን ድርጊት የምንሰጠው የድርጊት ምላሽ ነው፡፡ ማመንዘርም ለተሰማን የዝሙት ስሜት የምንሰጠው ምላሽ መሆኑን ልብ እንበል፡፡ ለምሳሌም የዳዊት ልጅ አምኖን የገዛ እኅቱ ትእማር ስትገባ ጡቷን፣ ደረቷን ስትወጣ ባቷን ተረከዟን እየተመለከት በሐጸ ዝሙት ተነደፈ፡፡ ከስሜት ሕዋሳቱ በአንዱ በዐይኑ አማካኝነት ወደ ዝሙት ስሜት ገባ፡፡ ከዚያም አልፎ ሰውነቱ ከሳ፤ ጓደኛው ኢዮናዳብ በመከረው ክ*ፉ ምክርም ተመርቶ እኅቱን አስነወራት፡፡ በስሜቱ የጋለበበት የዝሙት ጎዳናም በመጨረሻ ወንድሙ አቤሴሎም በክፋት እንዲነሣበትና ሕይወቱን እንዲነጥቀው ሆኗል፡፡ (፪ኛሳሙ.፲፫፥፩-፴፱)


መስ*ረቅም የስሜት ምላሽ ነው፡፡ አንድ የተራበን ሰው የፈለከውን በእጅህ ለማስገባት ምን ታደርጋለህ? ምግብ ይሰጡህ ዘንድ ትጠይቃለህ? የሻትከውን የራስህ ለማድረግ ጊዜ ትጠብቃለህ? ወይስ ትሰ*ርቃለህ? ብለን ብንጠይቅ፡-

ዛሬ በተግባር እንደሚታየው የብዙ ሰው ምላሽ ማታ*ለል፣ መስ*ረቅ፣ የጥቂት ሰው ምላሽ ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡ ስር*ቆት የስሜት ምላሽ መሆኑን እናስተውል፡፡ ክርስትና ለስሜት ፈጥነን ምላሽ ከመስጠት እንድንቆጠብ ያስተምረናል፡፡


ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምእመናን ያስተማረውን ትምህርት ማንሣቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ሐዋርያው “ነገር ግን እላለሁ÷ በመንፈስ ተመላለሱ፤ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፡፡ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፤ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ ከቶ አትችሉም” ይልና አያይዞም የሥጋ ፈቃዳትን (ሥጋዊ ስሜቶችን) ገልጦ “አስቀድሜም እንዳልሁ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም” ይላል (ገላ. ፭፥፲፯-፳፩)።


የሥጋ ምኞት የሥጋ ስሜት ነው፡፡ ዝሙት፣ ቅንአት፣ ምቀ*ኝነት ስሜቶች ሲሆኑ ቁጣ፣ አድመኝነት፣ መለያየት፣ መግ*ደል ደግሞ የስሜት ምላሾች ናቸው፡፡ ስሜቶቹም ሆኑ ምላሾቻቸው ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጭ እንደሚያደርጉ ተመልከቱ፡፡ ለስሜቶች ፈጥኖ ምላሽ ላለመስጠት መድኃኒቱ ራስን መግዛት ነው፡፡ ራስን መግዛት ማለት ስሜቶችን መቆጣጠር ማለት ነው፡፡ ስሜትን የመቆጣጠር ዓቅማችን የሚለካው ደግሞ ስሜቶቻችንን የሚቀሰቅሱና አሉታዊ ምላሾችን እንድንሰጥ የሚያስገድዱ ነገሮች ሲፈጠሩ ነው፡፡ ጀግና የሚወለደው በጦ*ርነት ሜዳ ላይ እንደሆነ ሁሉ፣ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ የሆነው ራስን መግዛት ገንዘብ ያደረገ ሰውም የሚገለጠው እንደ ጦ*ር የሚወጉ ክፉ ስሜቶች በሚሰሙት ጊዜ በሚያሳየው በጎና መንፈሳዊ ምላሽ ነው፡፡


ሰው ቅድሚያ ራሱን ካልተቆጣጠረና ስሜታዊነትን ካላስወገደ ተቋማትንም፣ ሀገርንም መምራት አይችልም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፤ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል” ይላል (ምሳ.፲፮፥፴፪)። ትዕግሥት ለቁጣና ለችኩልነት ስሜቶች የሚሰጥ በጎ ምላሽ ነው፡፡ በግል ኑሮው ለሚገጥመው ክ*ፉ ስሜት ቀስቃሽ ጉዳዮች ትዕግሥትን የሚያሳይ ሰው በጦር ሜዳ በጀግንነቱ ከሚታወቅ ሰው ይበልጣል፡፡ በመንፈሱ ማለትም በሐሳቡና በስሜቱም ላይ የበላይ ሆኖ ሐሳቡንም ስሜቱንም ምኞቱንም የሚቆጣጠር ሰውም ከተማን ከሚገዛ ሀገረ ገዥ ይበልጣል ይለናል ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡


ራስን መግዛት አንድ ስሜታችንን ለሚቀሰቅስ ሁነት ዐራት ዐይና ሆኖ በመገኘት ጉዳዮችን ከራስ፣ ከሌሎች፣ ከመንፈሳዊና ከሞራል ሕግጋት፣ ከማኅበረሰብ ባሕል ወግና ሥርዓት አንጻር መመልከት ነው፡፡ ራስን መግዛት ድርጊቶቻችን ምን አሉታዊና አዎንታዊ ምላሽ ይዘው ይመጣሉ? ብሎ መተንተን መቻል ነው፡፡ ሀገር የሚታወከው፣ ሐመረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በማዕበላት ፈተና የምትናጠው፣ ቤተሰብ የሚበተነው፣ ትዳር የሚፈርሰው ስሜታቸውን ብቻ እየተከተሉ በሚጓዙ ሰዎች ነው፡፡ የስሜት መንተክተክ ያበላሸውን ትዳር፣ ፖለቲካ፣ ሥርዓተ ማኅበረሰብ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያነጻ ግላዊና ማኅበረሰባዊ ስክነት ጠፍቷል ብለን መናገር እውነት እንጂ ሐሰት ወይም ግነት አይደለም፡፡


የአምላካችን የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን!!!


ምንጭ፦ https://eotcmk.org 

(ወደ ድህረ ገጹ በመግባት ተጨማሪ ያንብቡ)

Comments

Popular posts from this blog

Python Road map

 

Command on Run

 🔰 23 Important Commands in the RUN (Executer) List 🔹 The command dxdiag: Used to check all the specifications of your device.   🔹 The command cleanmgr: Opens the Disk Cleanup tool.   🔹 The command temp: Accesses temporary files, which we delete as they contribute to slowing down the computer.   🔹 The command regedit: Opens the Registry Editor.   🔹 The command calc: Opens the Calculator.   🔹 The command msconfig: A tool to access programs that run with Windows at startup and disable them to speed up the system.   🔹 The command scandisk: Used for disk checking.   🔹 The command cmd: Opens the Command Prompt for Windows.   🔹 The command defrag: Used to stop and defragment the hard drive.   🔹 The command taskman: Allows you to see what is open in the taskbar and manage it.   🔹 The command pbrush: Opens the Paint program in Windows.   🔹 The command debug: Used to ch...

Is it the end of lora?

 Is this the end of LoRA as a fine-tuning approach? Singular Value fine-tuning is here! We have a new paper in town called the "Transformers Squared". It promises to adapt any LLM to any task without external intervention.  The core idea of the paper is to use Singular Value Decomposition (SVD) to factorize the weight matrices of transformers. During training, we learn different singular values for different tasks. More specifically, we learn to scale the singular values for different tasks. Tasks can be as diverse as math reasoning or coding. The possibilities are endless. During inference, we do a two-pass inference. In the first pass, the LLM decides which "scale" to use for which task. In the second pass, the LLM adapts itself to be a specialist in the task and responds to our prompt. How cool is that? Paper Title: Transformer2: Self-adaptive LLMs Paper: https://sakana.ai/transformer-squared Blog: https://arxiv.org/abs/2501.06252 Video Explanation: https://youtu...