ምርጥ 11 የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች ልጠቁማችሁ!!
1) getintopc
https://getintopc.com
የተለያዩ ክራክ የተደረጉና ምርጥ ነጻ ሶፍትዌሮችን በማቅረብ የሚታወቅ ምርጥ ዌብሳይት ነው። በመሆኑም በዚህ ዌብሳይት የፈለጉትን ሶፍትዌሮችን በመፈለግ ማግኘት የሚያስችል በመሆኑ በብዙ ሰዎች ዘንድ ተፈላጊ ነው።
2) Download
https://download.cnet.com
የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡
3) FileHippo
https://filehippo.com
ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅመናል፡፡
4) ZDNet
https://downloads.zdnet.com
ይህ ሳይትም እንደሌሎቹ ብዙ የ ሶፍትዌር አማራጮችን የያዘ እና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሳይት ነዉ፡፡
5) Softpedia
https://www.softpedia.com
Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡
6) Tucows
https://www.tucows.com/downloads
ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡
7) FreewareFiles
https://www.freewarefiles.com
ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡
8) MajorGeeks
http://m.majorgeeks.com
ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ዩሰር ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡
9) FileCluster
https://www.bytesin.com
FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡
Comments
Post a Comment